Hot News
home Articles ከአማራ ማህበረሰብ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የተሰጠ መግለጫ

ከአማራ ማህበረሰብ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ማህበረሰብ ላለፉት 4 እና 5 አስርት አመታት  በተጨባጭ ከኢትዮጵያ   ፖለቲካዊ  ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች  እንቅስቃሴዎች ሁሉ እንዲገለል  ተደርጎ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።  ይህንን መገለል እና ጭቆና መሰረት አድርጎ በተነሳው እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተደረገ ባለው  ሁለንተናዊ  የአማራ ሕዝብ ትግል መነቃቃት የተፈጠረበት የአማራ ማሕበረሰብ ተወላጅ  በያለበት ክፍለ አለም እና ሃገር በመሰባሰብ  ፣ በመማማር እና ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች  ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።  በዚህም ረገድ በስደት ከሃግሩ ውጭ የሚኖረው የአማራ ህዝብ የየሃገሩ ሕግ በሚፈቅደው መሰረት  ኮሚውኒቲዎችን በመመስረት የሁለንተናዊው ትግል ደጋፊ ሆኖ ለመቀጠል ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ  ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኘው የአማራ ማህበረሰብ የዚህ አለማቀፋዊ የአማራ ህዝብ ንቅናቄ አካል ነው። ኮሚኒቲው ሃይማኖት ፣ እድሜ እና ጾታ የማይለይ ፤ ሁሉንም በአማራ ህዝብ ስም የቆሙ ድርጅቶች በእኩል ዓይን የሚመለከት ነው።  ከዚህም ባለፈ በአማራ ህዝብ ሰም የተመሰረቱ ድርጅቶች ቢቻል ወደ አንድ መጥተው የጉልበት ፣ የሀብት  እና የሃሳብ ብክነት ሳይኖር በአንድ ጥላስር በመሰባሰብ የአማራን ህዝብ ጥቅም  ሊያስከብር የሚችል   ጠንካራ ድርጅት ለመፍጠር ፤ ይህንን ለጊዜው ማድረግ ባይቻል እኳን ያሉት ጥቂት እና ጂምር ድርጅቶች ተደጋግፈው የሚታገሉበት ስርዓት እንዲፈጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴም  ሙሉ ድጋፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት የተነሳ ፤ በአንድ ወይም በሌላ ድርጅት እና ግለሰብ ተጽኖ ሰር እንዳይውድቅ በጥንቃቄ የተያዘ የንጹህ አማራ ወንድሞች እና እህቶች ስብስብ ነው።

ኮሚኒቲው እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 22 ፣ 2017 ዓ/ም  በሜሪላንድ ግዛት ፤ ሲልቨርስፕሪንግ ከተማ  ቬተራንስ ፕላዛ (1 Veterans Pl, Silver Spring, MD 20910) ታላቅ ታሪካዊ ጉባኤ ያካሂዳል። በዚህ የአማራ ህዝብ ታላቅ ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት ፣ ምሁራን እና አክቲቪስቶች ለምናደርገው እንቅስቃሴ የሞራል እና የሃሳብ ድጋፍ ከማበርከታቸውም በላይ የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ተሳታፊ እንዲሆኑ ላቀረብንላቸው ጥያቄ   በቃል ፣ በጹሁፍ እና በስልክ አማራዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ ይሁንታቸውን ገልጸውልናል።

ይሁን እንጅ ፤ የስብሰባውን ዋና ማስታወቂያ ለመልቀቅ የዳግማዊ መዐህድን  ድርጅታዊ መልሰ እየጠበቅን ባለበት ሰዓት  የተለቀቀው የዳግማዊ መዐህድን አርማ ያካተተው   ማስታወቂያ በአሰራር ስህተት ምክንያት የተፈጠረ  መሆኑን በጽኑ ማሳወቅ እንወዳለን።  ለተፈጠረው ስህተትም ሙሉ በሙሉ ኮሚኒቲው ሃላፊነቱን ይወስዳል ::  ወደፊት ለምንመሰርተው ጠንካራ የአማራ አንድነት እና አንድ ጠንካራ የአማራ የትግል ስርአት፤  የሚፈጠሩ ችግሮችን በሃላፊነት እና በመግባባት መፍታት የሚጠይቅ እንደሆነ እምነታችን ነው። የተለቀቀው   የዳግማዊ መዐህድ አርማ ያለበት ማስታወቂያ ለጊዜው እንዲነሳ የተደረገ መሆኑን እየገለጽን፤ ዳግማዊ መዐህድ የስብሰባውን ጊዜ መቃረብ ግምት ውስጥ በማስገባት በቃል እና በጹሁፍ በተደጋጋሚ ላቀረብንለት ጥሪ መልስ እንዲሰጠን በድጋሚ በትህትና እንጠይቃለን። ከዳግማዊ መዐህድ ድርጅታዊ መልስ ስናገኝ የድርጅቱን አርማ ያካተተ ማስታወቂያ እንደገና ለማሰራጨት ጥረት እናደርጋለን።

ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉም የአማራ ሕዝብ ዳገማዊ መዐህድ ጨምሮ ያሉትን ሁሉንም ድርጅቶች በቻለው ነገር ሁሉ መርዳት እና ማጠናከር ያለበት መሆኑን መግለጽ እንወዳለን።  ወደፊት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ የተቻለንን ያክል ጥንቃቄ የምናደርግ መሆኑን ቃል እየገባል፤ የአማራ ሕዝብ የቻለውን ሁሉ በማድረግ በዚህ ታሪካዊ እና ታላቅ ጉባኤ ላይ እንዲገኝ ጥሪያችንን በድጋሜ እናስተላልፋለን።

ማሳሰቢያ

  • ከኒውዮርክ፣ ኒውጀርሲ እና ፔንሲልቫኒያ በባልቲሞር በኩል መምጣት ለምትፈልጉ የአውቶብስ ቅንጅት ለማድረግ በ 1-888-730-6888 ደውለው ቢያናግሩን የማቀናጀት ድጋፍ እናደርጋለን።
  • ከኦሃዮ ልትመጡ ላሰባችሁ ወንድሞች እና እሕቶች ቦታ ካላችሁ እግረመንገዳችሁን ከሌሎች እስቴቶች ጋር መቀናጀት የምትችሉ በት ሁኔታ ቢፈጠር እንላለን።

“ .   .   .   የአማራ ሕዝብ ሁለንተናዊ ትግል ላይቀለበስ ተጀምሯል ፤ መጨረሻውም የአማራ እና የሌሎች ኢትዮጵያውያን ነጻነት ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል  .   .   .    ! ”

”  .   .   .  በ ጃንዋሪ 22፣  እግሮችሁሉ ወደ ዲሲ ያመራሉ    .   .   . !!”

የአማራ ማህበረሰብ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው !

You Might Also Like

Top