Hot News
home News ጉባኤውን በተመለከተ ለደረሱን ጥቆማዎች መግለጫ

ጉባኤውን በተመለከተ ለደረሱን ጥቆማዎች መግለጫ

የአማራ ኮሚውኒቲ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው  ለመጭው እሁድ ለምናደርገው ታላቅ ታሪካዊ ጉባዝግጅታችንን አጠናቀን እለቱን በጉጉት እየተጠባበቅን እንገኛለን !

የጉባኤው ቅድመ ዝግጅት በወንድሞች እና እህቶች ብርታት፤  በስልክ ፣ በአካል እና በሌሎች መንገዶች በምታደርጉልን ድጋፍ እንዲሁም በፈጣሪ እርዳታ በሚያስገርም ሁኔታ በተሳካ መንገድ እየተጠናቀቀ ይገኛል። ይህ ጉባኤ የአማራ ሕዝብ የሚያደርገውን  ፈታኝ ትግል  ሕዝባዊ መሰረት ለማስያዝ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

አማራ ከሆኑ ይሕ ታሪካዊ ጉባኤ በምንም ታምር ሊያመልጥዎ አይገባም የአማራ ሕዝብ በደል ያንገበገበዎት  አስተዋይ ህሊና ያለዎት የአማራ ወዳጅ ኢትዮጵያዊ ከሆኑ ይምጡ አጋርነትዎን በማሳየት ከጎናችን ይቁሙ ወደፊት ለሚኖረን ጤናማ እና ጠንካራ አንድነትም በጋራ መሰረት እንጣል ! ”

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህን ታሪካዊ ጉባኤ ለማደናቀፍ የሚፈልጉ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች አሉባልታ ወሬዎችን በማናፈስ  አንድነታችን ለማወክና ትግላችንን ለማደናቀፍ እየሞከሩ መሆኑን የአማራ ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ነገሮችን ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት አሉባልታ ወሬዎችን  ከሚያናፍሱት ግለሰቦች መካከል በአንድ ወቅት ወደ ማህበረሰባችን   በመምጣት ያለውን ጠንካራና  ግልጽ አሰራር ጠምዝዘው ለመቆጣጠር ፣  የግል አመለካከታቸውን እና የግል “ጥቅማቸውን” ለማስፈጸም የሞከሩ ነገር ግን ይህንን በሳል አሰራር ማለፍ ያልቻሉ ግለሰቦች እንደሆኑ ተረድተናል ።

ማህበረሰባችን  በሰራ እና በስራ ብቻ የሚያምን ለተራ ወሬዎች ቦታ የማይሰጥ  ቢሆንም ይህ አሉባልታ አንዳንድ ወንድሞች እና እህቶቻችን በየዋህነት እንዳያሳስት በማሰብ  “ሳይቃጠል በቅጠል” መባል  ያለበት መሆኑን ተገንዝበናል። በድጋሚ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የአማራ ማህበረሰብ እድሜ ፣ ጾታና ሐይማኖት  ሳይገድበው  ሁሉም አማራ የሚሰባሰቡበት ፣ የሚመካከሩበት እንዲሁም በጋራ እጅ ለጅ ተያይዘን ወደፊት የምንጓዝበት፤ ለሁሉም አማራ እና የአማራ ድርጅቶች ደህንነት ዘብ የሚቆም ስብስብ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን። ስራ ምግባርን ይገልጻል እንዲሉ ይህንን በስራችን ለማስመስከር  የሁላችሁንም ድጋፍ ተስፋ በማድረግ ጭምር እንተጋለን። ድርጅቱ የራስዎ መሆኑን ከልብ በማመን  ማንኛውንም አይነት መረጃ በፈለጉ ጊዜ የመጠየቅና አሰራርን ተከትሎ ማግኘት የአማራነት መብትዎና ግዴታዎም  ጭምር መሆኑን እየገለጽን ፤  ትግሉ የሁላችንም ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን እናሳስባለን።

የተከበራችሁ የአማራ ሕዝቦች፣ ለአማራ ህዝብ ዘብ የቆማችሁ ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንደነዚህ እይነት ፈተናዎች  በጋራ ለምናደርገው ትግል የመጀመሪያም የመጨረሻም አለመሆናቸውን በመረዳት ፤ ተምረንባቸው የምናልፍ እንጅ ለነጻነታችን የምናደርገውን ጉዞ ለደቂቃ የሚያደናቅፉ  እንደማይሆኑ ፤  ይባሱንም በቁጭት ለበለጠ ተጋድሎ እና መስዋትነት የሚያነሳሱ  መሆናቸውን በሙሉ ልብ ልናስገነዝባችሁ እንወዳለን።  የህዝባችን እምባ ለማበስ የሚደረገው የጋራ ጉዞም ለደቂቃ አይስተጓጎልም።

የአማራ ማህበረሰብ በዲሲ እና አካባቢው    .   .   .  !

 

 

You Might Also Like

Top