Hot News
home Articles የአማራ የማንነት ትግል፣ የህልውና ትግል እና የጠንካራ አደረጃጀት አስፈላጊነት

የአማራ የማንነት ትግል፣ የህልውና ትግል እና የጠንካራ አደረጃጀት አስፈላጊነት

የአማራ የማንነት ትግል፣ የህልውና ትግል እና የጠንካራ አደረጃጀት አስፈላጊነት
*******************************************
(በዳላስ የአማራ ማህበር ስብሰባ ላይ የቀረበ (1/28/2017)፡ አንባቢ አስተያየት እንዲያሰፍር ይጠየቃል፡፡)

በዚህ ጽሁፍ አማራ እያካሄደ ያለውን የሶስት ዘርፍ ጥምር ትግል ማለትም የማንነት ትግል፣ ማንነቱን መሰረት ያደረገ የህልውና ትግል እና ይህንን ትግሉን ዳር ለማድረስ የሚያግዘውን የጠንካራ ድርጅት አስፈላጊነት እዳስሳለሁ፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ ትግላችን መላውን አማራ በአንድ ጥላ ስር ማሰለፍ ይጠበቅበታል፡፡ በአንድ ጥላ ስር አሰባስቦም ለአንድ አላማ ማለትም ለአማራ ህልውና መከበር ማታገል ይጠበቅበታል፡፡ የአማራ አለማቀፍ ትግል በጠንካራ የአማራ ማንነት ላይ የተገነባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ጠንካራ ማንነት ሳይኖር የህልውና ትግልን ዳር የሚያደርሰውን ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለሆነም ጠንካራ ማንነት ግንባታ፣ እና በጣም የተደራጀ ጠንካራ ትግል የአማራን ህልውና ያስከብራሉ፡፡ ለዚህም እነዚህ ሶስቱ በተመጋጋቢነት ይሰራሉ፡፡

1. የአማራ ማንነት ጉዳይ

1.1. የአማራ ህዝብ አጠቃላይ ብሄራዊ አንድነት ማንነት
አማራ ብሄር ነው፡፡ የምናካሂደው እንቅስቃሴም የአማራ ብሄራዊ እንቅስቃሴ፣ የአማራ ብሄራዊ ትግል ወዘተ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ የአማራ ብሄር ማለትም አማራ እንደ ህዝብ በአንድ ወጥነት ማረጋገጫ ሳይንሳዊ መስፈርቶች በአማራነት ሊገልጹት የሚችሉ የማንነት አሀዶችን ያሟላል፡፡ እንደገናም በራሱ በአማራው ምልከታ-አለም አማራው ከጥንት ጀምሮ አማራነቱን ጠብቆ የኖረ ህዝብ እንደሆነ ለመረዳት አዳጋች አይደለም፡፡ የአማራን ማንነት ከእነዚህ ሁለት አውዶች አንጻር እንመልከት፡፡

1.1.1. የአማራ ህዝብ ምልከታ-አለም
የአማራ ህዝብ በራሱ ምልከታ-አለም ራሱን ከሌሎች ለይቶ የሚያይበት የማንነት መነጽር አለው፡፡ አማራው ስለራሱ ማንነት ያለው አመለካከት ከትውልድ ሀረግ ማንነት የሚመነጭ ነው፡፡ እኔ አማራ ነኝ ሲል በትውልድ ሀረጌ ወይም በዘሬ አማራ ነኝ ማለቱ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች አማራው ለራሱ ያለውን የአማራነት አመለካከት ለመጋፋት በሚል ብቻ አማራ መገለጫው ኢትዮጵያ ብቻ ነው በማለት ኢትዮጵያ የሚባል ዘር ያለ ለማስመሰል ይጥራሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ የአማራው አገሩ፣ የዜግነቱ መገለጫ እንጅ ዘሩ አይደለችም፡፡ ይሄ አማራ ዘሩ ኢትዮጵያዊ ነው የሚለው አባባል የብሄር ማንነታቸው ላይ ጠንካራ ትኩረት ለሚያደርጉ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተጻጻሪ እሳቤ ፈጣሪነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ አማራው ዘሩ ኢትዮጵያዊ ከሆነ እኔ ዘሬ ሌላ በመሆኑ ምክንያት አማራ/ኢትዮጵያዊ መሆን አልፈልግም የሚል አይነት አካሄድ እንዲሄዱ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በዚህም መነሻ አማራውን እንደ ጭፍላቂ ሲያስቆጥረው ቆይቷል፡፡ ምክንያቱም ኢትየጵያዊ መሆንን በቀጥታ አማራ መሆን አድርገው እንዲቆጥሩት እና እንዲቃወሙት ስላደረገ፡፡ የሌሎች ብሄር ልሂቃን ኢትዮጵያ ማለት ሌላው የአማራ ስም እንጅ እነሱን የሚያካትት አገር ወይም ዜግነት እንዳልሆነ እንዲያስቡ አድርጎአቸዋል፡፡ ይሄ በጨፍላቂነት ሲከሰስ የቆየው አካሄድ አማራን ብቸኛ የአገሪቱ ባለቤት እና ልዩ ተጠቃሚ ሆኖ እንዲቆጠር አድርጓል፡፡ በዚህም የተነሳ የራስዋ የአገሪቷ ሁኔታ አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ ሆኗል፡፡ ይሄ አስመሳይነት የተሞላበት እና ከእውነታው ጋር የማይገናኝ አካሄድ በመሰረቱ የጥቂት ልሂቃን አላማ እና ትርክት እንጅ የመላው አማራ ህዝብ አጀንዳ አይደለም፡፡ አማራ ዘሩ ኢትዮጵያዊ ነው የሚለው የተምታታ አካሄድ የአናሳ ልሂቃን (አማራ የሆኑም በአማራ ሽፋ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ) ፍላጎት እንጅ ህዝቡስ አማራነቱን ቀድሞ የሚያውቅ እና በልዩ ልዩ መንገድ የየሚገልጽ እና ኢትዮጵያን እንደሀገሩ የሚቆጥር ነው፡፡ የአማራ ዘሩ ኢትዮጵያዊ ነው የሚለው አባባል ሌሎች ብሄሮችን ችላ እንደማለት የሚቆጠር ነው፡፡ ይሄም አማራ ባልዋለበት በጨፍላቂነት እንዲከሰስ አድርጎታል፡፡ ኢትዮጵያን መቃረን አማራን እንደመቃረን እየተቆጠረ የአገሪቷ ደህንነት አደጋ ላይ የወደቀውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ እውነተኛው አነጋገር ግን ኢትዮጵያ የአማራ አገሩ መሆንዋ ነው፤ ከሌሎች ወንድምና እህቶቹ ጋር ሆኖ የሚጋራት አገር ናት፡፡ ከዛ በዘለለ የአማራ ዘር ልትሆን አትችልም፡፡ የአማራ ዘሩ አማራ ነው፡፡ በራሱ በአማራው አመለካከት እንዲህ ነው የሚገለጸው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአማራ ህዝብ አማራነቱ ከጎረቤት ብሄሮች አንጻር ይገለጻል፡፡ ለምሳሌ አማራ ማለት ኦሮሞ ያልሆነ ህዝብ፣ ትግሬ ያልሆነ ህዝብ፣ ሱማሌ ያልሆነ ህዝብ… ወዘተርፈ ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች ብሮች አማራን ከራሳቸው አንጻር በመመልከት አማራ ይሉታል፡፡ አማራም ከራሱ አንጻ በመመልከት በየብሄረር ስማቸው የይጠራቸዋል፡፡ እነዚህን አንድ የጋራ ነገር ከተገኘ ኢትዮጵያ አገራው መሆንዋ ብቻ ናቸው፡፡

1.1.2. የአማራ ማንነት በሳይንሳዊ መንገድ ሲተነተን
ሀ) ቋንቋ
አብዛኛው የአማራ ብሄር የአማርኛ ቋንቋ ይናገራል፡፡ ስለዚህ አማርኛ ቋንቋ የአማራን ብሄር ማንነት ገላጭ ነው ማለት ነው፡፡

ለ) የጋራ ታሪካዊ ሁኔታ
የአማራ ብሄር አንድ ወጥ ታሪካዊ ዳራዎች አሉት፡፡ ከጥንት እስካሁን ድረስ በጋራ ሲሳተፍበት እና ሲሰራው የቆየ አንድ አይነት ታሪካዊ ሁኔታ አለ፡፡ ይህም ማለት ታሪካዊ ሁኔታ የአማራን ብሄር አጠቃላይ ማንነት ይገልጻል ማለት ነው፡፡

ሐ) የጋራ ስነልቡናዊ ሁኔታ
የአማራ ብሄር አንድ አይነት አጠቃላይ የስነልቡና ሁኔታ አለው፡፡ ማለትም አማራ የሚያንጸባርቀው ስነልቡናዊ ባህርይ አንድ አይነት ነው፡፡ ይሄም የአማራ ብሄር አንድ አይነት ስነልቡናዊ መገለጫ አለው ማለት ነው፡፡

መ) የጋራ ማህበራዊ ሁኔታ
የአማራ ህዝብ ወይም ብሄር አንድ አይነት አጠቃላይ ማህበራዊ ክንዋኔዎችን የሚያደርግ እና በአንድ አይነት ማህበራዊ ክንዋኔዎች የሚገለጽ ህዝብ ነው፡፡ ስለዚህ የአማራን ብሄር አንድ አይነት ማህበራዊ ክንዋኔዎች ይገልጹታል፡፡

ሠ) ተመሳሳይ የመሬት አሰፋፈርና ስነብእል ሁኔታ
የአማራ ብሄር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ የሆነ የመሬት አሰፋፈር አለው፡፡ ይህም የመሬት አሰፋፈር ተመሳሳይ የሆነ መተዳደሪያ ሁኔታ እንዲኖር አድርጓል፡፡ ስለዚህ የመሬት አሰፋፈርና የአኗኗር ሁኔታ የአማራን ብሄር ማንነት ይገልጻል ማለት ነው፡፡

ረ) አንድ አይነት ተጠቂነት
ከሀ-ሠ የተዘረዘሩት ሳይንሳዊ የአማራን ብሄራዊ ማንነት ገላጭ ወይም የአማራ ብሄራዊ ማንነት መገለጫዎች ሲሆኑ በአማራ ህዝብ ልዩ ሁኔታ ረ ላይ የተቀመጠው ገላጭ በተጨማሪነት እንዲቀመጥ አስፈላጊ ሆኗል፡፡ አንድ አይነት ተጠቂነት በአሁኑ ልዩ ተጨባጭ ሁኔታ የአማራን ብሄር ገላጭ ተርጓሜ ነው፡፡ ህወሀት አማራ ጠላቴ ነው ወይም አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው ብሎ ሲነሳ በጠቅላላ የአማራን ብሄር ነው ኢላማው ያደረገው፡፡ አሁንም አለምንም ልዩነት በአንድ አማራነት ብቻ ነው እያጠቃ ያለው፡፡ ስለሆነም ጠላት ወይም አጥቂ አማራ ብሎ መስፈርት ሰርቶ ባስቀመጠው መሰረት እያጠፋ እስከሆነ ድረስ ያ የአማራነት ተጠቂነት ልዩ መለያ የአማራ ብሄራዊ ማንነት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ሌሎች የአማራ ጥላቻ የሚያጠቃቸው ቡድኖችም በተመሳሳይ መልኩ የአማራን ብሄራዊ ተጠቂነት ማንነት የመተርጎም አቅም ስላላቸው ከትግራዩ ድርጅት ጋር በአንድነት የሚታዩ ናቸው፡፡

ማስታወሻ፡- ከሀ-ሠ የተዘረዘሩት ውስጣዊ የማንነት መገለጫዎች ሲሆኑ ረ ላይ የተቀመጠው ውጫዊ ተርጓሚ አሀድ ነው፡፡ አማራነትን በመግለጽ ሂደት ውስጣዊ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆኑ ውጫዊ ሀይሎችም አስተዋጽኦ እያደረጉ ስለሆነ አማራን የተጠቂነት ወይም የኢላማነት ማንነቱ ይገልጸዋል፡፡

ሰ. አንድ አይነት እጣ ፋንታ፡- የአማራ ህዝብ (ብሄር) አንድ አይነት እጣ ፋንታ ብቻ ነው ያለው፡፡ እንደ አንድ ህዝብነት ተሳስሮ ከመኖር ውጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የለውም፡፡ ማለትም በእያንዳንዱ ተደራቢ ማንነቶች ላይ የተመሰረተ ሀሰት ላይ የተመሰረተ ህዝብ ከፋፋይ አካሄድ የህዝቡን እጣ ፋንታ በአንድ ገመድ መቋጠር ያላገናዘበ ነው፡፡ ይህ አንድ አይነት እጣ ፋንታ ዝም ብሎ ለወግ ማሳመሪያ የሚባል ሳይሆን በታሪክ የተረጋገጠ ነው፡፡ በአማራ ምድር የሚኖረው ማናቸውም ህዝብ ተነጣጥሎ የማያውቅ፣ አንድ ላይ በአንድ ህዝብነት በአንድ ፖለቲካዊ አስተዳደር ስር፣ በአንድ ታሪካዊ አውድ ስር እና በጠቅላላው ከላይ በተዘረዘረው የማንነት አሀድ ሁሉ አንድ ላይ የኖረ ኅዝብ ነው፡፡ አማራ አንድ አይነት እጣ ፋንታ አስተሳስሮት የቆየ ህዝብ ነው፤ ቀጣይ ኑሮውም አንድ ነው፡፡ ተለያይቶ ሊኖር የማይችል ህዝብ ነው፡፡ ስለሆነም ተጨባጭ እውነታ የሆነው የአማራ ህዝብ አንድ አይነት እጣ ፋንታ አማራን አንድ ያደርገዋል፡፡

1.2. የአማራ ብሄር ተደራቢ መገለጫዎች
ከላይ 1.1 ላይ እንደተገለጸው የአማራ ብሄር በጠቅላላው አንድ አይነት የሆነ ማንነት፣ መገለጫ ያለው ህዝብ ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ አጠቃላይ የአማራ ብሄር ማንነት መገለጫ ውስጥ ተደራቢ ማንነቶች አሉ፡፡ እነዚህ ማንነቶች አጠቃላይ የአማራውን ብሄር ማንነት በተዋጽኦ የገነቡ በመሆናቸው በምንም መንገድ ከአማራነት ውጭ ሊታዩ የማይችሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን የአማራው ህዝብ ደመኛ ጠላት የሆነው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት እነዚህን ተደራቢ ማንነቶች አማራውን ለመከፋፈል እና እርስ በእርሱ በማቃራን የራሱን ጸረ አማራ ፖለቲካዊ ሸፍጥ ለመፈጸም እንዳይጠቀምበት በመፍራት ቀድመን ለህዝብ፣ አባላት፣ ደጋፊና መሪዎች ግልጽ ግንዛቤ እንዲወስዱ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአማራ ተደራቢ ማንነቶች ላይ ድርጅቱ ግልጽ አቋም መውሰድ ይገባዋል፡፡ እነዚህ ተደራቢ ማንነቶችም አማራ፣ አገው አማራ፣ ቅማንት አማራ፣ ቤተ እስራኤል አማራ፣ ወይጦ አማራ እና አርጎባ አማራ ናቸው፡፡ እነዚህን ተደራቢ ማንነቶች ወይም መገለጫዎች ለመግለጽም አማራን እንደ ብሄር ስም እንወስደዋለን፡፡ እነዚህን ደግሞ በነገድነት ወይም ባጭሩ በተደራቢ ማንነት ልንወስዳቸው እንችላለን፡፡ በዚህም አነጋገር የአማራ ብሄር በነገድነት ወይም በተደራቢ ማንነት አማራን፣ አገው አማራን፣ ቅማንት አማራን፣ ቤተ እስራኤል አማራን፣ ወይጦ አማራን እና አርጎባ አማራን ያካትታል፡፡

ሀ) አማራ
ከላይ እንደተገለጸው አማራ የአማራ ብሄር አንድ አካል ነው፡፡ ይህ ነገድ ወይም ተደራቢ ማንነት አብዛኘውን ህዝብ የሚሸፍን በመሆኑ እንዲሁም የሁሉም አማራ ዋና ባህል ወይም ማንነት ስለሚገልጸው የዚሁ ነገድ መጠሪያ የአጠቃላይ ብሄሩ መጠሪያ ሆኗል፡፡ ይሁንና አማራ በአማራ ብሄር ውስጥ አንድ አካል ነው፡፡

ለ) አገው ወይም አገው አማራ
ከላይ እንደተገለጸው አገው ወይም አገው አማራ የአማራ ብሄር ክፍል ነው፡፡ አማራን የሚገልጸው ሁሉ የአገው አማራ ወይም የአገው መገለጫ ነው፡፡ ነገር ግን በተጨማሪነት የአገውኛ ቋንቋ ይናገራል፡፡ ከዚህ ቋንቋ ውጭ በሆነው ማንኛውም መስፈርት ከሌላው አማራ የተለየ ነገር የለውም፡፡

ሐ) ቅማንት ወይም ቅማንት አማራ
ከላይ እንደተገለጸው ቅማንት ወይም ቅማንት አማራ የአማራ ብሄር ክፍል ነው፡፡ አማራን የሚገልጸው ማናቸውም መለኪያ ይገልጸዋል፡፡ በስም ብቻ ቅማንት የሚለው ተጨማሪ ማንነት ቆይቷል፡፡ በጣም ውስን በሆነ ሁኔታ ቋንቋውም ይነገራል፡፡ ምናልባት ወደፊት ቋንቋው እንዲበለጽግ እና እንዲያንሰራራ ካልተደረገ በቀር በአሁኑ ደረጃ የቅማንትን ወይም የቅማንት አማራን ማንነት መግለጽ በሚችልበት ደረጃ ላይ አይገኝም፡፡ ስለሆነም አማራነት ቅማንትን ወይም ቅማንት አማራን ይገልጸዋል፡፡

መ) ቤተ እስራኤል አማራ
ቤተ እስራኤል አማራ የአማራ ብሄር አንዱ ክፍል ነው፡፡ ከአማራነት የተለየ መገለጫ የለውም፡፡ ሆኖም ወደእስራኤል አገር ከመሄዳቸው በፊት ፈላሻ ወይም ቤተ እስራኤል የሚል መጠሪያ ነበራቸው፡፡ ቋንቋቸው ግን አማርኛ ነበር፡፡ ሌላ የተለየ ማንነት አልነበራቸውም፡፡ አሁን ወደእስራኤል ከሄዱ በኋላ ግን ኋላኛው ትውልድ እብራይስጥኛን እንደ ዋና ቋንቋነት ይናገራል፡፡ አማርኛንም በተደራቢነት ይናገራሉ፡፡ አጠቃላይ ማንነታቸው ግን አማራነት ነው፡፡ ስለሆነም የአማራ ብሄር አንዱ ክፍል ናቸው፡፡

ሠ) አርጎባ አማራ
ከላይ እንደተገለጸው አርጎባ ወይም አርጎባ አማራ የአማራ ብሄር አንዱ ክፍል ነው፡፡ አማራን የሚገልጸው ሁሉ ይገልጸዋል፡፡ በውስን ደረጃ ቋንቋው ቢነገርም አብዛኛው ማንነታቸው አማራነት የሚገልጸው ነው፡፡

ረ) ወይጦ ወይም ወይጦ አማራ
ከላይ እንደተገለጸው ወይጦ በስም ወይጦ ከመባሉ ውጭ በማንኛውም መስፈርት አማራ ነው፡፡ ስለሆነም የአማራ ብሄር አካል ነው፡፡

ማስታወሻ፡- በዚህ ስር ሁለት ነገሮችን ማጤን ይኖርብናል፡፡
አንደኛ አንዳንድ ሰዎች ለምን ዝም ብለን አንድ አማራ ማለት ሲገባን እነዚህን ተደራቢ ማንነቶች ትኩረት አድርገን እንነጋገርባቸዋለን ይላሉ፡፡ ላይ ላዩን ሲታይ ትክክል ናቸው፡፡ አንድ አማራ እስከሆንን ድረስ ጉዳዩ ላይ ትኩረት መስጠቱ ብዙም አስፈላጊ ላይመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ይሄንን ተደራቢ ማንነት ልክ እንደ አማራ መከፋፈያ ዘዴ ለሚጠቀመው የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላት ወያኔና ጭፍራው በር ለመዝጋት ነው፡፡ ጉዳዩን ወያኔው አጀንዳ እስካደረገው ድረስ የእኛ ትኩረት ሰጥቶ መናገር እንጅ የሚጠቅመን በደምሳሳው ዝም ብሎ ማለፍ አይደለም፡፡ የወያኔን ውሸትም ማክሸፍ እና የህዝባችንን አንድነት ማስጠበቅ የምንችለው ይሄንን መሰል ሳይንሳዊ ትንታኔ በመስጠት ነው፡፡ ወያኔ ከዚህ ቀደም በቅማንት አማራ እንደሞከረው ለወደፊቱም አማራውን ለመከፋፈል እነዚህን መሰል ሸሮች ሊጠቀም ስለሚችል (ከወዲሁም አንዳንድ ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ) እኛ የአጀንዳው ባለቤቶች መሆናችንን ቀድመን ማረጋገጥ እና መፈትሄ አበጅተን መቆየት አለብን፡፡

ሁለተኛ እነዚህን ተደራቢ ማንነቶች አጠቃቀም ላይ ግለሰቦች የየራሳቸው አገላለጽ ነጻነት ወይ ምርጫ ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ብሄረተኛ አማራ አንድ አማራ ብቻ ብሎ ሊገልጽ ይችላል፡፡ አንዱ እኔ አገው አማራ ነኝ ወይም ቅማንት አማራ ነኝ ሊል ይችላል፡፡ አንዱ አገው ነኝ ወይም ቅማንት ነኝ ሊል ይችላል፡፡ ሁሉም ትክክል አገላለጾች ናቸው፡፡ በዚህም ጠራነው በዛ ስለ አንድ የአማራ ብሄር ነው እያወራን ያለነው እና ችግር አያመጣም፡፡ እንቅስቃሴያችንም ለእያንዳንዱ የአማራ ብሄር ግለሰብ ይህንን እና የመሳሰለውን ነጻነት መጋፋት የለበትም፡፡

ሶስተኛ ጉዳዩን ወደአደባባይ ራሳችን በዚህ ሳይንሳዊ መንገድ ማምጣታችን ዘላቂ የአማራ አንድነትን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት ያስችለናል፡፡ የወያኔን እና መሰሎቹን ጸረ አማራዎች ሴራም ቀድሞ ለማክሸፍ ያገለግለናል፡፡ በዚህ ሳይንሳዊ ትንታኔ ረገድም ላይ ላዩን ሲታዩ ትልቅ የሚመስሉት ተደራቢማንነቶች በውስጥ ይዘታቸው ከውጭ እንደሚታዩት አለመሆናቸውን ማረጋገጥ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡ ይሄውም ወያኔ የአስተዳደር ክልሎችን ሲመሰርት በአብዛኛው ቋንቋን መሰረት እንዳደረገው ሁሉ የአማራን ተደራቢ ማንነቶችም እንደዛው በመውሰድ ለመከፋፈል እና የተለያዩ አድርጎ ለማቅረብ ሲታትር ይታያል፡፡ በመሰረቱ ግን በአማራ ውስጥ ያሉት ተደራቢ ማንነቶች በራሳቸው ሊቆሙ የማይችሉ እና ከዋናው የአማራ ብሄር በምንም ተአምር ተነጥለው ሊታዩ የማይችሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ አንዳዶቹ ስም ብቻ ሲሆኑ የተቀሩት ደገሞ ከስም በተጨማሪ ቋንቋ አላቸው፡፡ ስም ደግሞ የሳይንሳዊ መስፈርትን ተከትለን የማንነት መገለጫ ልናደርገው የምንችለው አይደለም፡፡ ስለዚህ በአማራ ውስጥ ያሉት ተደራቢ ማነቶች ከብዙዎቹ መስፈርቶች አንድ ቋንቋን ብቻ ያሟላሉ፡፡ ያም ቢሆን በተደራቢነት የሚታይ እንጅ በራሱ ምልኡነት የሚታይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከአገው አማራ በቀር ሌሎቹ ቋንቋቸውን ለየእለት ተግባቦሽ የሚጠቀሙ አይደሉም፡፡ ስለዚህ አንድ መስፈርት ብቻ አንድን ተደራቢ ማንነት ከዋናው አማራ ብሄር የተለየ ሊያደርገው አይችልም፡፡ ከአማራ ጋር አንድ የሚያደርጉት በርካታ መስፈርቶች ሚዛን ይደፋሉና፡፡ ስለዚህ በምንም መስፈርት የአማራ ብሄር አንድ የአማራ ህዝብ ነው፡፡
ሰ) ሙያ-ነክ ማንነቶች
እንደሚታወቀው በአማራ ህዝብ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው የኖሩ ንኡሳን ማንነቶች ወይም ተደራቢ ማንቶች አሉ፡፡ እነሱም ለምሳሌ ሊቀመኳሶች፣ አንጥረኞች፣ የቆዳ ውጤቶች ሰራተኞች፣ እና ቀደም ባሉት ጊዜያት ፈላስሞች እና ሲራራ ነጋዴዎች የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ሁሉ በዋናው የአማራ ማንነት የሚብራሩ ተደራቢ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ራሳቸው አማራዎች ሆነው ሳለ በሂደት የተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ መገለጫቸው የሆኑ ማለት ነው፡፡

ሸ) ያለፉት አማሮች (የነገስታት ማንነት) እና በአሁኑ ጊዜ ሊኖራቸው የሚገባ ቦታ

የአማራ ብሄራዊ ትግል በህይወት ያሉትን ህልውናና ጥቅም ማስከበር እና ያለፉትን ክብር ማስጠበቅን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ በአማራ ትግል ውስጥ በህይወት ያለ ብቻ ሳይሆን በህይወት የሌለም ዋጋ አለው፡፡ ህዝባችን በህይወት ዘመኑ የሰራው ስራ ካለፈ በኋላ እንዲታወስ የሚፈልግ ጥልቅ ታሪክ-ወደድ ህዝብ ነው፡፡ ታላላቅ ሰዎችን ሲያስታውስ እንኳ “ስሙ እንደ ድንጋይ የተጎለተው” የሚለው ይሄንን ነገር በደምብ ያሳያል፡፡ ስለሆነም አዲሱ የአማራነት እንቅስቃሴ በጸረ አማሮች የሚዘለፉትን እና ያለ ሀጢአታቸው ስም የሚሰጣቸውን ያለፉትን ወገኖቻችን ስምና ዝና ማደስና ማስከበርን ያጠቃልላል፡፡

ነገስታት አማራ አይደሉም፣ ወይም ቅልቅል ነበሩ የሚለው አያስኬድም፡፡ እንደዛ የሚለው አስተሳሰብ የመነጨው የ60ዎቹ ትውልድ እየተባለ በተለምዶ የሚጠራው ትውልድ አማራው ጥፋተኛ ነው ብሎ ስላመነ እና ነገስታቶቹን ጥፋተኞች ናቸው ብሎ ስለሚከራከር ነው፡፡ ነገስታት አማራ አይደሉም ሲሉ ከጥፋተኛ ገዥዎች ራሳቸውን እንደማሸሽ ስለሚቆጥሩት ነው፡፡ ይህም ከእውነታው የራቀ፣ የድሮውን ዘመን ስርአት በአሁን ፖለቲካዊ ፍልስፍና እና የታሪክ አተያይ ረገድ ከማየት የመነጨ ነው፡፡ ነገስታት ግን ዘመናቸው በፈቀደው፣ በዘመናቸው በሚታወቀው መንገድ ነው የኖሩት፡፡ አሁን ላለው የኢትዮጵያ ብሄር ሁሉ ቋንቋና ማንነት ተጠብቆ መቆየት ትልቁን ሚና የተጫወቱት እነሱ ናቸው፡፡

ስላለፉት ገዥዎች የምንነጋገረው ጸረ አማራ የሆኑ ቡድች በከፈቱት የመከራከሪያ ነጥብ ሳይሆን በራሱ በሁኔታው አውድ መሰረት ብቻ ነው፡፡ በጸረ አማራዎች መነጽር እኛ ልናይ አንችልም፡፡ ያለፈውንም ሆነ የአሁኑን ሁኔታ ማየት የምንችለው በትክክለኛ መነጽር ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የአማራ ገዥዎች አቅደውና አስበው ህዝብ ለማጥፋት ወይም ለመጉዳት አልተንቀሳቀሱም፡፡ ባልዋሉበት እንዲከሰሱ የሚደርጋቸው የጸረ አማራ ቡድኖች መነጽር ነው፡፡ ያንን ሀሳዊ መነጽር ተውሰው የሚንሸዋረሩ የገዛ ወገኖቻችንም በጊዜ እውነተኛ መነጽር ቢገዙ ነው የሚሻላቸው፡፡

1.3. ከአማራ ብሄር እና ሌላ ብሄር የሚወለዱትን በተመለከተ
የአማራ ብሄራዊ ትግል ማንኛውንም አማራነቱን አምኖ የሚቀበል እንዲሁም የአማራነት ስሜት ያለውና በአማራነቱ ለጥቃት የተጋለጠውን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ በውስጣዊ ሁኔታዎች አማራ ሆኖ የተገኘው ብቻ ሳይሆን ውጫዊ ሀይሎችም በአማራነት ማእቀፍ ውስጥ ሊያስገቡት የሚችሉት ወገን በአማራነት ይገለጻል፡፡ ስለሆነም ከአማራና ከሌላ ብሄር የሚወለዱ ወገኖች አማራነታቸውን እስከፈለጉት ድረስ መገላጫቸውና ማንነታቸው ሆኖ ይቀጥላል፡፡

2. የአማራ ብሄራዊ ትግል ብቸኛው መፍትሄ ስለመሆኑ
ከላይ የተዘረዘሩትን ተደራቢ ማንቶችን በአንድ ወጥ የአማራ ብሄራዊ ትግልነት ማእቀፍ ስር አይተናቸዋል፡፡ ያ የሆነበትም ምክንያት በአማራ ምድር እና ለተበተነው አማራ ሁሉ ብቸኛው መፍትሄ የአማራነት እንቅስቃሴ ስለሆነ ነው፡፡ የአማራ ብሄረተኝነት ለመላው የአማራ ህዝብ በቂ መልስ ነው፡፡ እስከድል ድረስ ሁሉም እኩል ትግልና መስዋእትነት እንዲከፍሉ ያደርጋል፤ ከድል በኋላም አንድ አይነት እጣ ፋንታቸውን በአንድነት እንዲጎነጩ ያደርጋል፡፡ ከአማራ ብሄረተኝነት ውጭ የተሻለ መልስ እንደሌለም ራሱ ሁኔታው አስረጅ ነው፡፡ ይሁንና ትግሉ ተደራቢ ማንነቶችን እውቅና መስጠት እና መንከባከብ እንዲሁም ማበልጸግ ይጠበቅበታል፡፡ በዚህ መንገድ የተባበረ አንድ አማራ በአንድ ብሄራዊ ትግል ማእቀፍ ትግል ስር ተሰልፎ ቶሎ ድልን ያመጣል፡፡ ያም የሚሆንበት ምክንያት ይ መንገድ የጠላትን መግቢ ቀዳዳ ስለሚደፍነው እና ህዝቡ በሙሉ የራስ መተማመን እና በስነልቡና የበላይነት ትግሉን እንዲያካሂድ ስለሚግዘው ነው፡፡

3. ሀይማኖትን በተመለከተ የድርጅቱ አቋም
አማራ ብሄር ነው ስንል ያለምንም የሀይማኖት ልዩነት ነው፡፡ እስካሁን እንደሚታወቀው አማራ ኦሮቶዶክስ ክርስቲያን ብቻ ነው ብሎ ነጥሎ የመውሰድ ነገር ይታይ ነበር፡፡ ያ ግን ፈጽሞ ስህተት እና የጠላት ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ አማራ ክርስቲያን፣ እስላም እንዲሁም እምነት አልባውን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ በሌላ አነጋገር ሀይማኖት ለአማራ ማንነት መገለጫ ሆኖ አያገለግልም፡፡ ማለትም አንድ የተወሰነ ሀይማኖት አማራን አማራ አያደርገውም፡፡ ስለዚህ አማራ ስንል ከሀይማኖታዊ እሳቤ በጸዳ ሁኔታ መሆን ይገባዋል፡፡ አማራን በሀይማኖት ለመግለጽ ሲደረግ የቆየው የአማራን ማንነት አለመቀበል አንዱ አካ የሆነው ሀሳዊ ትርክት ነው፡፡ የተሳሳተ ስለሆነ ህዝባችን በተሳሳተ መንገድ ሊገለጽ አይገባም፡፡ አማራ ማንነቱ አማራ ነው፡፡ እንደማንኛውም ህዝብ ደግሞ ሀይማኖቶች አሉት፡፡ አማራን አማራ ያደረገው አማራነቱ እንጅ ሀይማኖቱ አይደለም፡፡

4. የአማራ ትግል አይነት እና አላማ
የአማራ ትግል የአማራ ትግል ተብሎ ሊገለጽ ይገባዋል፡፡ የአማራ አለማቀፋዊ ትግል ተብሎም በተለዋጭነት ሊገለጽ ይችላል፡፡ ተጋድሎ ነው ብለው ለሚናገሩትም ወገኖች ተቃውሞ ማቅረብ አያስፈልግም፡፡ ማንም ተጋድሎ ወይም ትግል ብሎ ሊጠራው ይችላል፡፡ የአማራ ህዝብ ትግል ወይም የአማራ ህዝብ አለማቀፋዊ ትግል ተብሎ ቢጠራ ግን ብዙውን ሊያስማማ ይችላል፡፡ በዋነኝነት ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል መሆኑ ነው፡፡ የህልውና ትግል ማለትም አማራው ራሱን እንደህዝብ ለማስቀጠል የሚያደርገው ትግል ነው፡፡ አማራው ዘሩ እንዳይጠፋ ለማድረግ የሚያደርገው ትግል ነው፡፡ ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ የመንግስት አወቃቀር አይነት፣ ህዝባዊ ውክልና፣ ስነ ብእል፣ ወይም ማህበራዊ እድገት የመሳሰሉት ጉዳዮች በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩ ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች የሚመለሱት ዋናው የህልውና ጥያቄ ሲመለስ ብቻ ነው፡፡ ከህልውና መከበር በፊት እነዚህ ጥያቄዎች እንደቀዳሚ አጀንዳ ሊወሰዱ አይገባም፡፡ ተከታይ አጀንዳዎች ናቸው፡፡

5. የብሄረተኝነትና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አስፈላጊነት

ጠንካራ ብሄረተኝነት የሚመጣው ከላይ በተዘረዘረውና በሌላ መንገድ የህዝቡን ስነልቡናዊ እና የስሜት ትስስር በማዳበር ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን ለአሁን ብቻ ሳይሆን ለሚመጣውም ዘመን በሁሉም ረገድ የተዘጋጀ ህዝብ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ አንድ አይነት አስተሳሰብ፣ አካሄድ እና ጠንካራ ትስስር ያለው ህዝብ የአሁኖቹን ጠላቶቹን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ለመጭዎቹ ዘመናትም የተዘጋጀ እና ራሱን በብቁ ሁኔታ የሚከላከል እንዲሆን ያስችለዋል፡፡ ስለዚህ የአማራነት እንቅስቃሴን እንመራለን፣ እናግዛለን የምንል ሰዎች ብሄረተኝነቱ ላይ ጠንካራ ስራ መስራት፣ አደረጃጀቱ ላይ ቁርጥ ያለ አቁዋም መያዝ እና ተጨባጭ አላማ ማስነገብን አስፈላጊነቱን አምነንበት መስራት አለብን፡፡ ይህንንም ለማገዝ እና አጠቃላዩን ትግል ለማፋጠን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያለው ትግል ጠቃሚ ነው፡፡ ማለትም የነጠረ አላማ ያለው ጠንካራ ድጅት ያስፈልጋል፡፡ ሰውን ማደራጀት የሚቻለው ደግሞ በአንድ አላማ ስር ለዛው አላማ እስከመስዋእትነት የሚያደርስ የአላማ ጽናት አንግቦ ነው፡፡ ይሄ መንገድ በተጓዳኝም አጋር አገርና ድርጅቶችን ለማግኘት ይረዳል፡፡

ጠንካራ ብሄረተኝነት እና ጥብቅ ድርጅታዊ ስነስርአት ያለው አደረጃጀት በቀላሉ ለድል ይበቃል፡፡ ከላይ በተዘረዘረው አስተሳሰብ ተቃኝቶ የሚደረገው ትግል የድል ቀናችንን ያፋጥናል፡፡ ይሄንን ጉዳይ አጽንኦት እድንሰጠው በአባታችን ግርማዊ አጼ ቴዎድሮስ የመጨረሻ መልእክት ልዝጋው፡፡ ለጄኔራል ናፒየር ከላከው ደብቤ በመጥቀስ፡፡ “የአገሬ ህዝብ ስራት ግባ ብየ ብለው እምቢ ብሎ ተጣላኝ፤” አንተ ግን ስራት ባለው ጦር አቸነፍከኝ፡፡

ምስጋናው አንዱዓለም
ከዳ/መዐሕድ

You Might Also Like

Top